መዝሙረ ዳዊት

" እግዚአብሔር አምላኩ የሆነለት ሕዝብ ብፁዕ ነው። " መዝ 32 ፦ 12

Thursday, May 24, 2012

ከቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ እና ማኅበረ ቅዱሳንን ከተመለከተው ውሳኔ ጋር በተያያዘ የእኔ ጥያቄዎች፦


ከቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ እና ማኅበረ ቅዱሳንን ከተመለከተው ውሳኔ ጋር በተያያዘ የእኔ ጥያቄዎች
  • የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ምን አይነት ጉባኤ ነው? … አባላቱ እነማን ናቸው? … ዝርዝር ተግባራቶቹ ምንድን ናቸው? … (የሃይማኖት ተቋማት ግንባር ፈጥረው የሚፈቱት ችግር ምን ዓይነት ነው?)
  • ቀደም ባሉ ምልዓተ ጉባኤያት የተወሰኑ ውሳኔዎች ተፈጻሚነታቸው ምን ይመስላል? … የውሳኔዎችን ተፈጻሚነት የሚከታተለው አካል ማን ይባላል? … (ለምሳሌ ባለፈው ምልዓተ ጉባኤ … ተነስቶ መካነ ቅርስ እንዲገባ ውሳኔ ያገኘው የአቡነ ጳውሎስ ሃውልት አሁንም እንደተገተረ አለ … ) … ውሳኔዎችን በማስፈጸም ሂደትስ የእኛ የምዕመናን ድርሻ ምንድን ነው? …
  • ማኅበረ ቅዱሳን ከሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ አመራሮች (አመራር?) ጋር እንጅ ከመምሪያው ጋር ምን ችግር ነበረበት እና ነው ከመምሪያው ሥር የሚወጣው? …
  • … ቀድሞ የተሰጠው ደንብና የአሰራር መዋቅር ከወቅቱ ሁኔታ ጋር እንደገና ተመርምሮና ተሻሽሎ እስኪቀርብ ተጠሪነቱ ለብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ ሆኖ አመራር በመቀበል እየሰራ እንዲቆይ የሚለው ውሳኔ የደስታ ምንጭነቱ እንዴት ነው?
  • ድኀረ ማኅበረ ቅዱሳንስ (ማኅበሩ ከሥሩ ከወጣ በኋላስ) የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ እንደቀድሞው ነው የሚቀጥለው? … የሰንበት ት/ቤቶችን በሚገባ ለመምራት አቅሙን እንዴት ሊገነባ … ምን አይነት ነገሮችን ሊያስተካክል ይገባዋል? … ነው ወይስ ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር ከሚገባው ንትርክ ውጭ ሌላ የአቅም ችግር የለበትም?
  • የዋልድባ ገዳምን ጉዳይ ምልዓተ ጉባኤው እንዴት ባለ መረዳት ቢረዳው ነው እንዲህ ትኩረት የነፈገው? …

No comments:

Post a Comment