መዝሙረ ዳዊት

" እግዚአብሔር አምላኩ የሆነለት ሕዝብ ብፁዕ ነው። " መዝ 32 ፦ 12

Sunday, April 17, 2011

ታዘብኩዎት

ታዘብኩዎት

በርግጥ ...
ፊደል ቆጥሬያለሁ
ስምን በማጣመም ቅፅል ተምሬያለሁ
የግስን ተውሳክ በደንብ እለያለሁ
ስለዚህም እርስዎን አመሰግናለሁ።

ቢሆንም ...
ስለ ቋንቋ ዲስኩርዎት
በጣም ታዘብኩዎት
ቋንቋን እያወቁት ... ያግባባል ያስማማል
ይወለዳል ያድጋል ... ያረጃል ይሞታል
ብለው ብቻ ሲያልፉት ... አለማፈርዎት
ያግባባል ያሉት ያጣላል ... 
ያድጋል ያሉት ያሳጥራል ...
ይሞታል ያሉት ያጋድላል ...

ግን እርስዎ ... የቋንቋን ክፉ ሊያወሩ
ለምን እጅግ ፈሩ?

17/02/98
ለአማርኛ መምህሬ ማስታወሻ ብጤ
 (የራሳቸውን ቋንቋ ክብር ፤ የሌላውን በማሳነስ የሚገልጡ አንዳንድ አገራራሚ ሰዎችን በማሰብ የተጻፈ)

No comments:

Post a Comment